Arada Hibret

Self-Governance

Arada Addis Ababa Children’s Alliance – is a political movement established by Addis Ababa children to answer the political questions of the people of Addis Ababa. A year has passed since Arada started its political struggle, and in this one year, it has successfully carried out grass-root mobilization work. The main cause of the multifaceted suffering and loss of existence that is happening to the people of Addis Ababa is political. Arada believes that the people of Addis Ababa have been exposed to the oppression, suffering and general danger of existence as the basic human rights of self-government and political power and representation have been taken away from the people of Addis Ababa since the day the constitution was ratified. Therefore, Arada is working to answer the political questions of the people of Addis Ababa by using a wide and continuous popular movement and civil disobedience as a struggle strategy.

About

Addis Ababa Children’s Union

Why is struggle necessary?
Addis Ababa is a wonderful city that has gone through the process of urbanization for thousands of years and has created and integrated urbanism in a unique Ethiopian context. What makes Addis Ababa unique as a city is that it nurtures and celebrates many Ethiopian and international identities. Urbanism, in its international character, is the melting pot of different identities through the willing interaction of different identities by the owners of the identities. But Addis Ababa has created a broad and acceptable identity called Addis Abebe from the interaction that occurs with respect to the various identities within it.

Addis Ababa’s international development dates back thousands of years, and Addis Ababa as a city has made a significant contribution to the Pan-African Movement and other African countries’ struggle for independence. For this reason, the main office of the African Union is located in Addis Ababa. In addition, Addis Ababa is one of the few diplomatic center cities in the world. Apart from its international influence, Addis Ababa is a city that has an indelible mark on the history of Ethiopia. Addis Ababa is Ethiopia’s economic engine and political heartbeat.

It is a recent memory that the EHRDP government, which came to power after the fall of the military Derg regime, forcibly imposed the constitution on the people of Addis Ababa, which is the source of universal problems for Addis Ababa. The people of Addis Ababa have been deprived of political power and political rights, and they have become vulnerable to many social, political and economic problems because they do not own their own land.

However, on the day after the change, the officials who turned into explosives and became shields are participating in drafting and implementing destructive plans against the people of Addis Ababa. Officials who don’t understand that it originates from the political symbol and their cadres who are bound by interests. They have been working to create a non-cooperative and distrustful society by tearing apart our social values.

We are seeing that they are trying to make a city that creates a feeling of alienation by destroying our stories and depriving it of sentimental value. By denying political representation, they are throwing our urgent questions that are the death knell for Addis Abebe into the trash. Individuals in the city by giving them high power, by establishing a network of unstyled robbery and corruption on the people who owe the city to them, have brought us to the edge where we cannot win the daily life. If he can do all this abuse, why don’t we add to it with the arrogance of asking the creator for mercy, the political intervention and forceful action taken to divide the religious institutions has angered us.

Looking at the system and the many abuses that the system is doing from the bottom up, we do not believe that the system and administration that governs Addis Ababa will do any constructive work for the benefit of the public in the future. Because of this, we found that giving more time to the systematic abuse that is happening to us is like accepting oppression as amen, so we were forced to start a public peaceful struggle movement representing Addis Ababa.

Vision

The vision of our movement is to reclaim the political rights and power that the people of Addis Ababa have been deprived of by the regime through a broad peaceful public struggle and to control the administrative, social and security structures to enable our city to be completely managed by the people of Addis Ababa – self-governance.

The people of Addis Ababa as an independent political community, the economic and other social assets that we contribute to our country of Ethiopia are enormous, but we have never been involved in the politics of our country, nor have we been influential. Even worse, it is a public fact that our existence as a political society has been denied and that there are political forces working to destroy our existence and identity as their political goal. The current regime can be cited as an example. Therefore, the people of Addis Ababa should be an active participant and influencer in the politics of our country along with our fellow Ethiopians.

Goal

Although Addis Ababa has made a great contribution to Ethiopia’s economy and politics, it has not received the right political power to represent Addis Ababa as the constitution allows. We will work to restore representation.

Addis Ababa Children’s Union, which is guided by the attitude of “country means people”. As a result, Adis Abebe is guaranteed to live in peace; Adis Abebe is safe.

Enforcing the right to produce wealth and property and not denying any services due to identity, language, opinion and religion etc.

To enable Addis Ababa to get a fair trial before the law.

To ensure that Addis Ababa’s right to get a job without discrimination from the job opportunities created in Addis Ababa is respected.

To stop the inhumane eviction of warrs from their homes, which does not follow law and order. The widespread government corruption in Addis Ababa to stop.

Creating a stable economic system in Addis Ababa.

Addis Abebe is self-sufficient by using the right given by the constitution. It participates in multi-disciplinary activities, such as coordinating public movements and taking legal measures to ensure administrative rights.

The line of struggle chosen by the Addis Ababa Children’s Union to fight the oppressive system.

Systematic, modern and constantly evolving.

The children of Addis Ababa is a public peaceful struggle strategy that can bring down the roots.

All Ethiopians who believe in unity, rule of law, equality and independence.

We invite you to support our movement.

አራዳ የአዲስ አበባ ልጆች ህብረት

መግቢያ

ትግል ለምን አስፈለገ ?
አዲስ አበባ ለብዙ ሺህ ዘመናት በከተሜነት ሂደት ውስጥ ያለፈች እና ከተሜነትን በተለየ
ኢትዩጵያዊ አውድ የፈጠረች እና ያዋሀደች ድንቅ ከተማ ናት። አዲስ አበባ እንደ ከተማ ለየት የሚያደርጋት ብዙ ኢትዩጵያዊ እና አለምአቀፋዊ ማንነቶች አዋህዳ በመያዝ ማሳደጓ እና ማክበሯ ነው። ከተሜነት በአለምአቀፍ ባሕሪው የተለያዩ ማንነቶችን በማንነቶች ባለቤቶች በሚደረግ ፍቃደኛ መስተጋብር የተለያዩ ማንነቶችን ወደ አንድ ማንነት መውሰዱ
ነው(melting pot) ። አዲስ አበባ ግን በውስጧ የሚገኙ የተለያዩ ማንነቶች ከእነእሴቶቻቸው አክብራ በመያዝ ከዚህ ጋር ተያይዞ ከሚፈጠረው መስተጋብር አዲስ አበቤ የሚባል ሰፊና ቅቡል ማንነት መፍጠሯ ነው። አዲስ አበቤ አለምአቀፍ እድምታዋ ከብዙ ሺህ ዘመናት በፊት የነበረ ሲሆን። ለፓን አፍሪካ ንቅናቄ እና ሌሎች የአፍሪካ አገራት ለነፃነት በሚያደርጉት ትግል አዲስ አበባ እንደ አንድ ከተማ ጉልህ አስተዋጽኦ አድርጋለች። ለዚህም የአፍሪካ ሕብረት ድርጅት ዋናው ጽሕፈት ቤት መቀመጫው አዲስ አበባ ይገኛል። አለፍ ሲልም አለም ውስጥ ካሉ ጥቂት የዲኘሎማሲ መነሐሪያ ከተሞች ውስጥ አንዷ አዲስ አበባ ናት። አዲስ አበባ ከአለምአቀፍ እደምታዋ በተጨማሪም በኢትዩጵያ ታሪክ ላይ ሊፋቅ የማይችል አሻራ ያላት ከተማ ናት። አዲስ አበባ የኢትዩጵያን ምጣኔ ሐብት ሞተር የምታንቀሳቅስ እና የፖለቲካውም የልብ ትርታ ናት። ከወታደራዊው ደርግ አገዛዝ መዉደቅ ተከትሎ ወደ ስልጣን መንበሩ የመጣው የኢሕዴግ መንግሥት- ለአዲስ አበባ ሁለእንተናዊ ችግር ምንጭ የሆነውን ሕገ-
መንግሥት በግዴታ አዲስ አበባ ሕዝብ ላይ መጫኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። የአዲስ አበባ

ሕዝብ የፖለቲካ ስልጣን እና የፖለቲካ መብት መነፈጉ ሳያንሰው የገዛ መሬቱ ባለቤት
ባለመሆኑ ለዘርፈ ብዙ ማሕበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ ሆኗል።
ሆኖም በለውጡ ማግስት ፈንጂ ቀልበን ጋሻ ሆነን ወንበር የስጠናቸወ ባለስልጣናት የአዲስ
አበባ ህዝብ ላይ አጥፊ እቅዶችን በማርቀቅ እና መሪ ሆነው በማስፈፀም ላይ እየተሳተፉ
ይገኛሉ አልፈው ተርፈው የመንግስት ተቋማትን በመሳሪያነት በመጠቀም ስርአታዊ በደል
እያደረሱብን መሆኑን በብዙ መልኩ ስንገልፅ ቆይተናል የሚሰማ የኖራል በሚል ኢትዮጵያዊ
ጨዋነት ይህም የሆነው አዲስ አበቤ ታጋሽነት እና ይቅር ባይነት ከስልጡን አመልካከት
የመነጨ መሆኑን ያልተረዱ ባለሥልጣናት እና በጥቅም የተሳስሩ ካድረዎቻቸው · ማህበራዊ
እሴቶቻችንን በመበጣጠስ የማይተባበር የማይተማመን ማህበረስብ ለመፍጥር ሲሰሩ
ቆይተዋል · ታሪኮቻችንን በማፈራረስ sentimental value በማሳጣት የማናቃት እንግዳነት ስሜት የምታሳደር ከተማ ለማድረግ ሲስሩ እያየን ነው · የፖለቲካ ውክልና በመንፈግ ለአዲስ አበቤ የሞት ሽረት የሆኑ አንገብጋቢ ጥያቄዎቻችንን ወደ ቆሻሻ ቅርጫት የሚጥሉ ግለስቦች የከተማይቱ ከፍተኛ ስልጣን በመስጠት ጥሮ ግሮ ከተማይቱን ላቀናት ባለውለታ ህዝብ ላይ ቅጥ የለሸ ዝርፊያ ሙስና መረብ በመዘርጋት የቀን ኑሮውን ማሽነፍ የማንችልበት ጠርዝ አድርሶናል · በሃቅ ላይ ተመኩዘው ጥያቄ ያቀረቡ ፡ የተከራከሩ ፡ ኢፍትሃዊነትን የተቃወሙ አዲስ አበቤ ህጻን አዋቂ አረጋውያን ሳይለዩ ድምጻችንን ለማፈን እስር እና ግድያ መንግስታዊ መልስ ሆንዋል · ይህንን ሁሉ በደል ከቻለ ለምን አንጨምርለትም በሚመስል እብሪተኘነት አስተሳስብ ፈጣሪውን ምህረት የሚማፀንበት የሀይማኖት ተቋማቶቹን ለመከፋፈል የተወሰድው ፖለቲካዊ ጣልቃገብነት እና የሃይል እርምጃ አስቆጥቶናል ከላይ በጥቂቱ
የጠቀስናቸው እና ስርአቱ ከስር ከስር የሚስራቸውን በርካታ ግፎቸ ስንመለከት አዲስ አበባን የሚያስተዳድራት ስርአት በቀጣይ ለህዝብ የሚጠቅም አንዳችም ገንቢ ስራ ይሰራል ብለን አናምንም ፣ በመሆኑ እየደረሰብን ያለውን ስርአታዊ በደል ተጨማሪ ግዜ መስጠት ጭቆናን አሜን ብሎ እንደመቀበል ሆኖ ስላገኘነው አዲስ አበቤን የሚወክል ህዝባዊ ስላማዊ ትግል ለመጀመር ተገደናል።

ራዐይ
1- የንቅናቄው ራዐይ የአዲስ አበባ ሕዝብ በአገዛዙ የተነጠቀውን የፖለቲካ መብትና ስልጣን ሰፊ በሆነ በሰላማዊና ሕዝባዊ ትግል በማስመለስ የከተማችንን
የአስተዳደር፣ ማሕበራዊና ፀጥታ መዋቅሮችን በመቆጣጠር ከተማችንን ሙሉ በሙሉ በአዲስ አበባውያን ማስተዳደር መችል ነው። Self govrenance.
2- የአዲስ አበባ ሕዝብ ራሱን እንደ ቻለ እንደ አንድ የፖለቲካ ማሕበረሰብ
ለኢትዩጵያ ሀገራችን የምናበረክተው የኢኮኖሚና ሌሎች ማሕበራዊ እስቴች
እጅግ ግዙፍ ናቸው። ነገር ግን ለአገራችን በምናበረክተው ልክ መጠን የአገራችን
ፖለቲካ ላይ ተሳታፊም፣ ተጽእኖ ፈጣሪም ሆነን አናውቅም። ይባስ ብሎም እንደ
አንድ የፖለቲካ ማሕበረሰብ ሕልውናችን የተካደ እና ሕልውናችንን እና ማንነታችንን ማጥፋት የፖለቲካ ግባቸው አድርገው እየሰሩ ያሉ የፖለቲካ ሐይሎች እንዳሉ የአደባባይ ሐቅ ነው። እንደ ማሳያ አሁን ያለው አገዛዝ መጥቀስ ይቻላል። ስለሆነም የአዲስ አበባ ሕዝብ በሚገባን መጠን እና ልክ የአገራችን ፖለቲካ ላይ ከሌሎች ኢትዩጵያውያን ወገኖቻችን ጋር በመሆን ንቁ ተሳታፊ እና ተጽእኖ ፈጣሪ መሆን።

ግብ

  1. አዲስ አበቤ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ውስጥ ታላቅ አስተዋጽኦ ቢኖረውም
    ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው ልክ ትክክለኛ አዲስ አበቤን የሚወክል የፖለቲካ ስልጣን
    አላገኘም
    ስለሆነም የአዲስ አበባ ልጆች ሕብረት ያለ አግባብ ያጣነውን የፖለቲካ
    ውክልና ለማስመለስ እንስራለን።
  2. የአዲስ አበባ ልጆች ሕብረት “ሃገር ማለት ህዝብ ነው” አመለካከት የሚመራ
    በመሆኑ – አዲስ አበቤ በስላም የመኖር ዋስትና መረጋገጥ፣ – አዲስ አበቤ ያለስጋት
    ሃብት ንብረት የማፍራት መብት ማስከበር ፣ – በማንነት በቋንቋ በአመለካከት
    በሃይማኖት ወዘተ ምክንያት ማንኛውንም አገልግሎቶች እንዳይነፈግ ማድረግ –
    አዲስ አበቤ በህግ ፊት ሚዛናዊ ዳኘነት እንዲያገኝ …… – በአዲስ አበባ ከሚፈጠረው
    የስራ እድል አዲስ አበቤ ያለ አድልዎ ብቁ የሆነበት ቦታ ስራ የማግኝት መብት
    እንዲከበር ማድረግ – አዲስ አበባ ከምታመነጨው ሃብት አዲስ አበቤ ያለ አድሎ
    መገለል ብደር እና ጥቅማጥቅሞችን እንዲያገኘ ማድረግ
    – ህግ እና ስርአት ያልተከተለ
    ከስብአዊነት የራቀ መልኩ የሚካሄደውን ዋሪዎችን ከቤታቸው ማፈናቀል
    እንቅስቃሴ ማስቆም
    – በአዲስ አበባ ተንስራፍቶ የሚታየውን መንግስታዊ ሙስና
    ማስቆም – በአዲስ አበባ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ስርአት መፍጠር።
  3. አዲስ አበቤ በህገመንግስቱ የተስጠውን መብት አንቀፀ በመጠቀም ራስን በራስ
    የማስታዳድር መብት ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑ ህዝባዊ ንቅናቄችንም
    በማስተባበም ሆነ ህጋዊ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ሁለገብ ተግባሮች ላይ ይሳተፋል

ማጠቃለያ
ግፈኛ ስርአት ለመታገል የአዲስ አበባ ልጆች ሕብረት የመረጠው የትግል መስመር ስልታዊ ፣ ዘመናዊ እና ራሱን ከሁኔታዎች ጋር (constantly evolving ) በመለዋውጥ ስርቱን ማንበርከክ የሚችል ህዝባዊ ስላማዊ የትግል ስልት ነው የአዲስ አበባ ልጆች
ሕብረት በህግ የበላይነት እኩልነት እና ነጸነት የሚያምኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ
ንቅናቄያችንን እንዲደግፉ ጥሪ እናቀርባለን።